ቢዝነስ

በጋምቤላ ክልል 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

By Melaku Gedif

July 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ባለፉት 11 ወራት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የክልሉን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በተለይም አሁን ላይ በክልሉ የተፈጠረው አስተማማኝ ሰላም የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዲጨምር ማድረጉን ነው ያስረዱት፡፡

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት በኢንዱስትሪ፣ በግብርና እና በአገልግሎት ዘርፎች ለመሰማራት ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 223 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

አልሚ ባለሃብቶቹ 17 ሺህ 196 ሔክታር የመስሪያ ቦታ መረከባቸውን ጠቁመው÷ ወደ ሥራ እንዲገቡ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ባለሃብቶቹ ሥራ ሲጀምሩ ለ11 ሺህ 14 ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!