አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለሁለተኛው ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን አድርጓል፡፡
በዚሁ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በሰጡት ማብራሪያ፤ 350 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነቱ ከወለድ ነፃ የሆነ በረዥም ጊዜ የሚከፈል ብድር ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣቱን ተከትሎ የመጣ የብድር ስምምነት ነው ብለዋል፡፡
አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ለማጠናከር እና ለማስፈፀም ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ እንደሆነም ተመላክቷል።
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እጅግ በጣም ውጤታም መሆኑ ስለታመነበት ስምምነቱ ተፈፅሟል ነው ያሉት፡፡
በሚቀጥለው ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ከዘንድሮ የበለጠ ውጤት ያመጣል ሲሉም ገልፀዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!