አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር አንዳንድ ያልተጠበቁ ውጤቶችን እያስመለከተ ሩብ ፍፃሜ ላይ ደርሷል፡፡
በአዲስ አቀራረብ 32 ቡድኖችን ተሳታፊ በማድረግ ውድድሩን የጀመረው የ2025 የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር አሁን ስምንት ቡድኖች ብቻ ቀርተውታል።
በውድድሩ ብዙ ርቀት ይጓዛሉ ተብለው የተጠበቁት ማንቼስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።
ማንቼስተር ሲቲ በሳውዲው ክለብ አል ሂላል፤ ኢንተርሚላን ደግሞ በብራዚሉ ፍሉሚኔንሴ ተሸንፈው ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
የክለቦች ዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ሲጀምሩ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አል ሂላል ከፍሉሚኔንሴ ይጫወታል።
በሌላ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ፓልሜራስ ከቼልሲ፤ ፒኤስጂ ከባየርን ሙኒክ እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከቦርሲያ ዶርትሙንድ ይገናኛሉ፡፡
ሪያል ማድሪድን ከቦርሲያ ዶርትሙንድ በሚያገናኘው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ሁለቱ ወንድማማቾች ጁድ እና ጆቤ በተቃራኒው የሚፋለሙበት ዕድል ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ጆቤ ቤሊንግሃም በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከቱ ቡድኑ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በቅጣት ያመልጠዋል።
በዚህም ምክንያት ጆቤ ከታላቅ ወንድሙ ጁድ ቤሊንግሀም ጋር በክለቦች ዓለም ዋንጫ ዉድድር ላይ በተቃራኒው የመጫወት ዕድል የለውም፡፡
የፓልሜራስ እና ቼልሲ አሸናፊ ከአል ሂላል እና ፍሉሚኔንሴ አሸናፊ እንዲሁም የፒኤስጂ እና ባየርን ሙኒክ አሸናፊ ከቦርሲያ ዶርትሙንድ እና ሪያል ማድሪድ አሸናፊ ጋር በግማሽ ፍፃሜው የሚገናኙ ይሆናል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!