የሀገር ውስጥ ዜና

አጀንዳ ከሚሰበሰብባቸው መንገዶች አንዱ የምሁራን ጥናት ነው – መሥፍን አረዓያ (ፕ/ር)

By Abiy Getahun

July 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ ከሚሰበስብባቸው መንገዶች መካከል የምሁራን ጥናት አንዱ ነው አሉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አረዓያ (ፕ/ር)።

የታሪክ ባለሙያዎች ማህበር እና የሰላምና ደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦቻቸውን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል፡፡

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አረዓያ (ፕ/ር) እንደገለፁት፤ ኮሚሽኑ አጀንዳ ከሚሰበስብባቸው መንገዶች አንዱ የምሁራን ጥናት ነው።

ተደራጅተው የቀረቡትን የምሁራን ምክረ ሀሳቦች ለምክክር ሂደቱ እንጠቀምበታለን ነው ያሉት፡፡

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ የምሁራኑን የጥናት ምክረ ሀሳብ በአስተባባሪነት የመራው ፒስ ኤንድ ላይፍ ኢንስቲትዩት ሲሆን ከ29 ዩኒቨርሲቲዎች 45 ምሁራንን አሳትፏል።

በስምንት ዓበይት ጉዳዮች የተደራጀው የጥናት ምክረ ሀሳብ የልዩነት ምንጮችንና መፍትሄዎችን በተመለከተ ዝርዝር ሀሳቦች ተካተውበታል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የጥናት ሰነዱን የላይፍ ኤንድ ፒስ ኢኒስቲትዩት አመራሮች፣ የታሪክ ባለሙያዎች ማኅበር ተወካይ እና የሰላምና ደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ተገኝተው በሰነዱ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!