የሀገር ውስጥ ዜና

የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል አመራርና አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

By Hailemaryam Tegegn

July 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል አመራርና አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጋር በመሆን በየካ ተራራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል በተሰየመው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሀገር ከመጠበቅ ጎን ለጎን በአካባቢ ጥበቃ ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

በምስክር ስናፍቅ