የሀገር ውስጥ ዜና

“ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ከሩቅ የማስቀረት ብቃት ያለው ሠራዊት ተገንብቷል” ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

By Melaku Gedif

July 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ከሩቅ የማስቀረትና ብሄራዊ አደጋ ቢከሰት በብቃት መቀልበስ የሚችል ሠራዊት ተገንብቷል አሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ15ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ከሁሉም የጦር ክፍሎች የተወጣጡ ከፍተኛ መኮንኖች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የሰራዊቱ አመራሮች፣ አምባሳደሮችና ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።

የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉጌታ አምባቸው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖች በቀጣይ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም የሚያስችል ስልጠና ወስደዋል።

የወታደራዊ አመራር ሥልጠናው ዘመኑ የሚጠይቀውን ዕውቀት በመጨበጥ ኢትዮጵያን በላቀ ደረጃ ማገልገል እንዲችሉ የሚያዘጋጃቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ኮሌጁ ከኢትዮጵያ በተጨመሪ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ወታደራዊ አመራሮችን እያፈራ ያለ ተቋም መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በየሻምበል ምህረት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!