ስፓርት

ካይል ዎከር ለበርንሌይ ፈረመ

By Melaku Gedif

July 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የማንቼስተር ሲቲ የክንፍ ተከላካይ ካይል ዎከር በርንሌይን በ5 ሚሊየን ፓውንድ ተቀላቅሏል፡፡

የ35 ዓመቱ ዎከር ባለፈው የውድድር ዓመት ለማንቼስተር ሲቲ 15 ጊዜ የተሰለፈ ሲሆን÷ በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ጣልያኑ ኤሲሚላን በመሄድ መጫወቱ ይታወሳል፡፡

በኢቲሃድ ቆይታው 17 ዋንጫዎችን ያሳካው ዎከር ÷ በ2023 የውድድር ዓመት ሲቲ ባለ የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት ሲሆንም የቡድኑ አባል ነበር፡፡

በፈረንጆቹ 2017 ለዜጎቹ ከቶትንሃም ሆትስፐር የፈረመው ካይል ዎከር 319 ጨዋታዎች ላይ መሰለፉ ተመላክቷል፡፡

በ2024 ከሊጉ ወደ ሻምፒየንሺፑ የወረደው በርንሌይ ባለፈው የውድድር ዓመት ዳግም ወደ ሊጉ ማደጉ ይታወቃል፡፡

በርንሌይ ቀደም ሲል አክሴል ቷንዜቤ፣ ሃርትማን፣ ማክስ ዌስ እና ሉም ቻውናን የመሳሳሉ ተጫዋቾችን እንዳስፈረመ ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ማንቼስተር ዩናይትድ የ18 ዓመቱን የመሃል ተከላካይ ዲዬጎ ሊዮንን ከፓራጓዩ ክለብ ሴሮ ፖርቴኖ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

በአቤል ንዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!