የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ የኮሞሮስ ነጻነት በዓል ላይ ለመታደም ሞሮኒ ኮሞሮስ ገቡ

By Melaku Gedif

July 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ50ኛው የኮሞሮስ ነጻነት በዓል ላይ ለመሳተፍ ሞሮኒ ኮሞሮስ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሞሮኒ ልዑል ሰይድ ኢብራሂም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኮሞሮስ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችው ሰኔ 29 ቀን 1967 ዓ.ም ሲሆን÷ በነገው ዕለት የምታከብረው 50ኛውን የነጻነት በዓሏን ነው።

በነጻነት በዓሉ ለመታደም ፕሬዚዳንት ታዬን ጨምሮ የሴኔጋል፣ ታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ ማዳጋስካር፣ ሞሪታንያ እና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ኮሞሮስ መግባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporationFacebook www.facebook.com/fanabroadcastingTelegram t.me/fanatelevisionWebsite www.fanamc.comTikTok www.tiktok.com/@fana_televisionWhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainmentFacebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporateTikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainmentAmharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!