አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብርን በጅግጅጋ ከተማ አስጀምረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሕብረተሰቡ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የኢትዮጵያን የመረዳዳት እና የመተባበር ባህል ይበልጥ የሚያጠናከር ተግባር መሆኑንም አውስተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የችግኝ ተከላ፣ የአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ፣ ደም ልገሳ፣ ነጻ ሕክምና እና ሌሎች ሰው ተኮር ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስገንዝበዋል፡፡
ስለሆነም ዜጎች በዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቶ ሙስጠፌ ዕለቱን በማስመልከት በጅግጅጋ የችግኝ ተከላና የጽዳት መርሐ ግብር ማከናወናቸውንም የክልሉ አካባቢ ጥበቃና የገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ የአየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ሂላል መሃመድ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!