ስፓርት

በ41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን አትሌት መሰረት ገብሬ እና ገመቹ ያደሳ አሸነፉ

By Yonas Getnet

July 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሴቶች መሰረት ገብሬ እና በወንዶች አትሌት ገመቹ ያደሳ አሸንፈዋል።

41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

በዚህም በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን በመወከል የተሳተፈው አትሌት ገመቹ ያደሳ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል።

እንዲሁም በሴቶች የማራቶች ውድድር ከኦሮሚያ ክልል አትሌት መሰረት ገብሬ በቀዳሚነት በመግባት በ41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን አሸንፋለች።

ለውድድሩ አሸናፊዎች የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሚኪያስ ምትኩ