አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን።
በክልሉ ኡራ ወረዳ በ74 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የመስኖ መሰረተ ልማት ሥራ ጀምሯል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት፤ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማሻሻል እና ምርታማነትን ለማሳደግ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ብቻ በክልሉ 11 የመስኖ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ገልጸው፤ አርሶ አደሩ የመስኖ መሰረተ ልማትን ተጠቅሞ በማልማት የምግብ ዋስትናን ማረጋጥ እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በበኩላቸው፤ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ዛሬ ለአገልግሎት የበቃው የፀንፀሎ መስኖ ፕሮጀክት የአካባቢውን አርሶ አደር ከባህላዊ የመስኖ ሥራ የሚያላቅቅ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ በአካባቢው የሚገኙ ሶስት ቀበሌዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረው፤ ከ800 በላይ ነዋሪዎች በመስኖ ልማት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በመስኖ ፕሮጀክቱ አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!