አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን ለማስቀጠል በትጋት ይሰራል አሉ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ኃይሉ አዱኛ።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ባለፉት አምስት ቀናት በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኙ አምስት ዞኖች ስኬታማ ጉብኝት አድርገዋል።
አቶ ኃይሉ አዱኛ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ቡድን በቦረና፣ በምዕራብ ጉጂ፣ በምስራቅ ቦረና፣ በጉጂ እና በባሌ ዞኖች የመስክ ምልከታ ማድረጉን ገልጸዋል።
በዚህም ከተረጂነት ለመላቀቅ ምርታማነትን ለማሳደግ የተያዙ ግቦችን አፈጻጸም በመመልከት ውጤታማ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ የተሰጠበት መሆኑን አንስተዋል።
በተለይም በቦረና፣ በምዕራብ ጉጂ፣ በምስራቅ ቦረና እና በጉጂ ቆላማ አካባቢዎች ለዘመናት ሳይለሙ የቆዩ መሬቶችን በማልማት ለውጥ መምጣት ተጀምሯል ነው ያሉት።
በዚህም አካባቢዎቹ የስንዴ ምርትን ጨምሮ ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን በክላስተር በማምረት ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ሥራዎችን ውጤታማነት በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ ለቀጣይነቱም በትጋት ይሰራል ብለዋል።
ለዚህም በክልሉ መንግስት እየተገነቡ የሚገኙ የፊና የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶች አጋዥ መሆናቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በሌላ መልኩ በክልሉ መንግስት ተደራጅቶ ወደ ስራ የገባው የቀበሌ አደረጃጀት ለሕዝቡ በቅርበት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የተረጋገጠበት ጉብኝት ነው ብለዋል።
በዚህም አደረጃጀቱ የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች በመፍታት ላይ እንደሚገኝ የታየበት ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!