የሀገር ውስጥ ዜና

 የብሪክስ መድረክ ዓለም አቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Mikias Ayele

July 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ ዓመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል ብለዋል።

የበለጠ እኩልነት እና ፍትኅ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን በማለት ገልጸው፤ የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡