የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የሚታየው ለውጥ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን የሚያነቃቃ ነው – ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ

By Melaku Gedif

July 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ እያየነው ያለነው አስደናቂ ለውጥ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን የሚያነቃቃ ነው አሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ፡፡

ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ በአዲስ አበባ ዛሬ በተጀመረው የአፍሪካ የሥራ እድል ፈጠራ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በአዲስ አበባ የተወሰኑ ርቀቶች መንቀሳቀስ የኢትዮጵያን ለውጥ በግልጽ ያሳያል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እየታየው ላለው ኢኮኖሚያዊ እድገትም ሆነ አጠቃላይ መሻሻል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር አሻራ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

ይህ የኢትዮጵያ ለውጥ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን የሚያነቃቃ መሆኑንም ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ እንደዚህ ባለ ለውጥ ውስጥ ሆና ማየት ለሁላችንም ደስታ ይሰጣል ብለዋል።

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን በማጠናከር የሥራ እድል ፈጠራን በማሳደግ አኅጉራዊ ልማትን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው÷ የኢኮኖሚ ማሻሻያን መሰረት ባደረገና በልዩ አመራር በየዓመቱ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል እየተፈጠረ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ለሥራ እድል ፈጠራ የተሰጠው ልዩ ትኩረት እያደገ የመጣውን የወጣቶች ቁጥር በልዩ መልኩ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!