አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ግንባታቸው ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ የልማት ፕሮጀክቶችን ሊያስመርቅ ነው፡፡
በአልማ የስትራቴጂና ኢኖቬሽን ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበረ መኩሪያ በሰጡት መግለጫ÷ ማህበሩ በክልሉ ሁሉም ዞኖች የትምህርት፣ ጤና እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክቶች መገንባቱን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ከሐምሌ 1 አስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበረውን የአልማ ሳምንት ምክንያት በማድረግ የሚመረቁ ሲሆን÷ ለመሰረተ ልማቶቹ ከ645 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ መጪ ተደርጓል ብለዋል፡፡
አልማ ባለፉት 32 ዓመታት ከአባላትና ከአጋር አካላት በተገኘ ሃብት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው÷ አሁን ላይ ከ4 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ መደበኛ አባላት እንዳሉት አንስተዋል፡፡
ማኅበሩ ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ7 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት በማሠባሠብ የተለያዩ ሥራዎችን ማከናወኑን አመልክተዋል፡፡
በምናለ አየነው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!