አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን ለመታደም ስታዲየም ይገኛሉ፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሜት ላይፍ ስታዲየም በመገኘት የፍጻሜውን ጨዋታ እንደሚመለከቱ ዴይሊ ሜል ስፖርት ዘግቧል፡፡
በአዲስ አቀራረብ 32 ቡድኖችን አሳትፎ ውድድሩን የጀመረው የ2025 የክለቦች ዓለም ዋንጫ አሁን ላይ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡
በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው ውድድሩ ከአየር ንብረት እና ከተመልካች እጥረት ጋር በተያያዘ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡
አስቀድሞ ፍጻሜውን የተቀላቀለው ቼልሲ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከሚጫወቱት ሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂ አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይፋለማል፡፡
የክለቦች ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በሜት ላይፍ ስታዲየም የፊታችን እሑድ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!