የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጀማል አሕመድ በደቡብ ካሎሪና ተወካዮች ም/ቤት እውቅና ተሰጣቸው

By Melaku Gedif

July 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ በደቡብ ካሎሪና ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡

አቶ ጀማል እውቅና የተሰጣቸው ሚድሮክ በእርሳቸው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በተለያዩ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንድትሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው፡፡

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በግብርና እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በመሰማራት ኢትዮጵያ በዘርፉ አመርቂ ውጤት እንድታስመዘገብ ጉልህ ሚና መጫወቱ ተመላክቷል፡፡

የቡና፣ ሻይ ቅጠልና ሌሎች ምርቶችን ለውጪ ገበያ በማቅረብ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንድትሆን ማስቻሉም ተጠቅሷል፡፡

ከግብርና ባሻገር በኢንዱስትሪና ሌሎች ዘርፎች የተሰማራው ሚዲሮክ ኢትዮጵያ ለጀመረችው አካታችና ዘላቂ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ መገለጹንም ድርጅቱ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!