ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቴክሳስ የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ጉዳት ጎበኙ

By Mikias Ayele

July 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ በቴክሳስ የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ጉዳት ተመልክተዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት አደጋው ከመድረሱ በፊት ባለስልጣናቱ ማስጠንቀቂያ አልሰጡም በሚል ከህዝብ የቀረበውን ቅሬታ ለማጣራት እና ለተጎጂዎች እርዳታ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እያደረጉ ባሉት ጉብኝት በቴክሳስ ከሚገኙ ባለስልጣናት እና የአደጋ ምላሽ ሰጪ ሰራተኞች ጋር እየተወያዩ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ባለፈው ሳምንት አርብ በደረሰው የጎርፍ አደጋ 120 ሰዎች ሲሞቱ 160 ሰዎች ደግሞ እስካሁን እንዳልተገኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ