ዓለምአቀፋዊ ዜና

የህንዱ አውሮፕላን አደጋ የነዳጅ መቆጣጠሪያ በመበጠሱ ምክንያት መከሰቱ ተነገረ

By Mikias Ayele

July 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአንድ ወር በፊት በህንድ አሕመዳባድ የተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የአውሮፕላኑ የነዳጅ መቆጣጠሪያ በመበጠሱ ምክንያት የተከሰተ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡

በህንድ ቦይንግ 787- 8 የመንገደኞች አውሮፕላን በመከስከሱ 241 ሰዎች ሲሞቱ አንድ ሰው በህይዎት መትረፉ ይታወሳል፡፡

የአደጋውን ምክንያት ሲያጣራ የቆየው ኤር ኢንዲያ በዛሬው እለት የአውሮፕላኑን የአደጋ ምክንያት ሪፖርት ይፋ አደርጓል፡፡

እንደ ኤር ኢንዲያ ሪፖርትም የአደጋው ምክንያት አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት የነዳጅ መቆጣጠሪያዎቹ ተበጥሰው እንደነበር እና በዚህም ከተነሳ ከጥቂት ሴኮንዶች በኋላ ሞተሩ በመጥፋቱ መከስከሱን አስታውቋል፡፡

ከአደጋው አስቀድሞ የአውሮፕላኑ ሁለት አብራሪዎች የአውሮፕላኑ የነዳጅ መቆጣጠሪያ ለምን አልሰራም በሚል ሲነታረኩ የሚያሰማ የድምፅ ቅጅም መገኘቱን ገልጿል፡፡

ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ ኤር ኢንዲያ ከህንድ ባለስልጣናት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ