የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ

By Hailemaryam Tegegn

July 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀምረዋል።

የካቢኔ ጉዳዮችና የሴክተሮች ክትትል ሚኒስትር ዴዔታ አቶ አክሊሉ ታደሰ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ33 ሚሊየን ብር ወጪ አንድ ሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና አምስት ሞዴል የገጠር ቤቶችን ይገነባል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ረገድ ተጨባጭ ለውጥ የተገኘበት ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የመንግስትን ሰው ተኮር ተግባራት ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ በዚህም ብዙዎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

በፍሬው አለማየሁ