አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር አከናውኗል፡፡
በተጨማሪም ኢባትሎ በአስተዳደሩ ያስገነባው የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገ ሲሆን÷ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስም ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የኢባትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)÷ ተቋሙ የወጪ እና ገቢ ንግድን ከማሳለጥ ባሻገር በተለያዩ ዘርፎች ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ሶስት ዓመታት ከ77 ሺህ በላይ ችግኝ በመትከል የተራቆቱ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገገሙ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡
በ38 ሚሊየን ብር ወጪ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ት/ቤት ኢባትሎ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው÷ ኢባትሎ በድሬዳዋ አስተዳደር እያከናወናቸው ለሚገኙ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!