አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሕዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተጨባጭ ምላሽ ለመስጠት አመራሩ በትጋት ሊሰራ ይገባል አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ፡፡
የክልሉ ውኃና ኢነርጅ ቢሮ ሲያከናውነው የቆየውን የሕንጻ እድሳት፣ የውስጥ አደረጃጀትን ለሥራ ምቹ የማድረግ እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች አስመርቋል።
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የቢሮውን የሕንጻ እድሳት፣ የውስጥ አደረጃጀት እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
አቶ አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት÷የቢሮ እድሳት፣ የመልሶ ግንባታ እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ለሥራ ምቹ አካባቢ ከመፍጠር ባሻገር ሥርዓትን በመዘርጋት ረገድ ወሳኝ ሥራ የተከናወነበት ነው ብለዋል።
በዚህም ቢሮው ለውስጥ ሠራተኞች እና ለውጭ ደንበኞች የተመቸ፣ ሳቢና ማራኪ የሥራ አካባቢ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡
ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና ውጤታማ የሃብት አጠቃቀምን መሠረት በማድረግ የፕሮጀክቶችን ወቅታዊ አፈጻጸም ለመከታተል እና ለማሥተዳደር የተዘረጋው ሥርዓት ለሌሎች ተቋማት አርአያ እንደሚሆን አመላክተዋል።
“ሕዝባችን አስቸኳይ እና ተጨባጭ ምላሽ የሚፈልግ የመሠረተ ልማት ጥያቄ አለው” ያሉት ርዕሰ መሥተዳደሩ÷ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የመጠጥ ውኃ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።
የሕዝብን ጥያቄ እንደ ዕድልም፤ እንደ ተግዳሮትም የሚቆጥር መሪ መኖር እንዳለበት ጠቁመው÷ ሁል ጊዜ ልማትን ለሚናፍቅ ሕዝብ ሌት ተቀን የሚተጋ መሪ መሆን ያስፈልጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!