የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ የማጠቃለያ ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ

By Mikias Ayele

July 14, 2025

አዲስአበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ሥራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንዲሁም የዋና ጽህፈት ቤት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ሥራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ሪፖርት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።