አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር 50 ነጥብ 7 ሚሊየን እንቁላል እና 47 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ወተት ተመርቷል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡
በቢሮው የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ ይርጋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ በክልሉ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡
የሌማት ትሩፋት የዜጎችን የማምረት አቅም በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የወተት፣ ማር፣ ዶሮ እና ዓሣ መንደሮችን በማደራጀት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
በሌማት ትሩፋት አደረጃጀት ለወተት 48፣ ለዶሮ 148፣ ለማር 46 እና ለዓሣ 33 መንደሮችን በማደራጀት በትኩረት መሰራቱን ነው ያስረዱት፡፡
የተደራጁ ማህበራትን ምርታማነት የሚያሳድጉ የቴክኖሎጂ እና የተሻሻሉ ዝርያዎችን የማቅረብ ሥራ ተከናውኗል ነው ያሉት፡፡
በበጀት ዓመቱም 50 ነጥብ 7 ሚሊየን እንቁላል፣ 47 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ወተት፣ 4 ሺህ 236 ቶን ማር እና 5 ሺህ 895 ቶን የዓሣ ምርት መገኘቱን አብራርተዋል፡፡
ይህም የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ በዘርፉ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር በትኩረትና በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!