አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለ2017/18 የምርት ዘመን ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በዩኒዬኖችና ሕብረት ስራ ማሕበራት በኩል ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል።
የክልሉ የሕብረት ስራ ማሕበር ኤጀንሲ ለምርት ዘመኑ ከ10 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከውጪ ለማስገባት አቅዶ እስካሁን ከ7 ሚሊየን 200 ሺህ ኩንታል በላይ ማስገባቱን የአጀንሲው ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ፊሮምሳ አበራ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ውስጥ ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ በዩኒዬኖችና ሕብረት ስራ ማሕበራት በኩል ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን አንስተው÷ የቀረው በዩኒዬኖች መጋዘን እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
የአፈር ማዳበሪያን ህገወጥ ግብይት ለማስቀረት የክትትልና ድጋፍ ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
ባለፉት ዓመታት የተስተዋሉ ህገወጥ ተግባራትን ለማስቀረት የግብይት ሂደቱ በዲጂታል መንገድ እንዲሆን በማድረግ ችግሮቹን መቅረፍ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የአረም መድኃኒቶች በክልሉ የግብርና ሕብረት ስራ ፌዴሬሽን በኩል መቅረቡን ገልጸው÷ 2 ሚሊየን ሊትር የአረም ማጥፊያ ኬሚካል መዘጋጀቱንና 700 ሺህ ሊትር ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱን አስረድተዋል።
በተመሳሳይ 457 ሺህ ኩንታል የምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን 386 ሺህ ምርጥ ዘር ማከፋፈል መቻሉንም አቶ ፊሮምሳ አንስተዋል፡፡
በፀሐይ ጉልማ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!