አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አበረታች ውጤት አስገኝቷል አሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ፡፡
አቶ አደም ፋራህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤትና የክልልና የከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤቶች አመራሮች በድሬዳዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ድሬ ስቲል ፋብሪካን፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን፣ በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባውን ቤተ መጽሐፍት፣ የኮሪደር ልማት፣ የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስቴዲየምና ሌሎች ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በከተማዋ በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ግዙፍ የልማት ሥራዎች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳቸው እጅግ የላቀ ነው።
በድሬዳዋ ከተማ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተምሳሌት በመሆን በግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ስኬት መመዝገቡን ነው ያብራሩት፡፡
በዚህም ከውጭ ሀገር ሲገቡ የነበሩ ምርቶችን በመተካት የውጭ ምንዛሪ ማዳን እና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አመልክተዋል፡፡
ከተማዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ያለው የኮንቬንሽን ማዕከል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስገንዝበዋል፡፡
የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ በከተማ አስተዳደሩ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የተከናወነው ሥራ ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ብለዋል።
ድሬዳዋ ከተማ በልማትና በሰላም ያስመዘገበችውን ተምሳሌትነት አጠናክራ መቀጠል እንዳለባትም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡