አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ7 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የጤና አገልግሎቶች ይሰጣሉ።
በበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ መርሐ ግብር ከ5 ሺህ 500 ዩኒት በላይ ደም እንደሚሰበሰብ እና 50 ሺህ ለሚሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የምርመራ እና ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡
የወባ እና ኮሌራ በሽታዎች ስርጭትን መቆጣጠር እና መከላከል ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራሉ ያሉት አቶ ሳሙኤል÷ የደም ግፊት፣ ከአንገት በላይ ህክምና፣ የዓይን፣ የቆዳ፣ የስኳር ነጻ ምርመራና ህክምና የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ጤና ኬላዎችና ጤና ቢሮ ከ150 ሺሕ በላይ ለምግብነት የሚውሉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እንደሚካሄድ ነው የገለጹት፡፡
ለአረጋውያን እና ወላጅ ያጡ ህጻናት ህክምናና እና እንክብካቤ እንዲሁም የጤና ትምህርቶችን መስጠት፣ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ እና እድሳት ስራዎች እንደሚሰሩም አመልክተዋል፡፡
በጤናው ዘርፍ በሚሰጡ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከመንግስት እና ሕዝብ ሊወጣ የሚችል ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለማዳን እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በመርሐ ግብሩ የዓይን፣ የቆዳ፣ ከአንገት በላይ፣ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቶች፣ ጠቅላላ ሀኪሞች፣ የጤና መኮንኖችና ነርሶችን ጨምሮ ከ7 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!