አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጅሊስ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ አብዱላዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር) እንዳሉት፤ “ምርጫ ለጽኑ ተቋም” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ከሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።
የመራጮች ምዝገባው በመጪው እሁድ ሐምሌ 13 ቀን 2017 የሚጠናቀቅ በመሆኑ ለመራጭነት ያልተመዘገበው ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የመጅሊስ አመራሮች የቅድመ የምርጫ ሂደቱ 98 በመቶ መከናወኑን ገልጸው፤ ምርጫው ከነሐሴ 9 እስከ 11 ቀን 2017 በመላው ሀገሪቱ ምርጫው ይካሄዳል ብለዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ ይመራኛል የሚለውን አመራር ለመምረጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ከተካሄደ በኋላም የሚመረጠው የመጅሊስ አመራር ለቀጣይ አምስት ዓመታት ህዝበ ሙስሊሙን የሚመራ ይሆናል።
በፈቲያ አብደላ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!