የሀገር ውስጥ ዜና

የአቡ ዳቢ በረራ አየር መንገዱ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር የማስተሳሰር ጥረቱን ያጠናክራል

By Yonas Getnet

July 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአቡ ዳቢ በረራ መጀመር አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር ነው አሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው።

አየር መንገዱ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዋና ከተማ አቡ ዳቢ በትላንትናው ዕለት አዲስ በረራ ጀምሯል።

የአየር መንገዱ የመጀመሪያ ተጓዦች አቡ ዳቢ ዛይድ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በአውሮፕላን ማረፊያው እና በኢትሃድ ኤርዌይስ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት÷ አየር መንገዱ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር አዲስ አበባን እንደ ማዕከል በመጠቀም ወደ ተለያዩ መዳረሻዎች እየበረረ ይገኛል ብለዋል።

የአቡ ዳቢ በረራ መጀመርም ይህንን የሚያጠናክር መሆኑን አንስተው÷ ከኢትሃድ ጋር በመተባበር የተጀመረው የቀጥታ በረራ ለተሳፋሪዎች ምቹ ሁኔታን እንዲሁም ለንግድ እና ባህል ትስስር ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡ ዳቢ ያስጀመረው አዲሱ በረራ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያለውን የበረራ መዳረሻ ወደ አራት ያሳደገ መሆኑም ተመልክቷል።

በዘመን በየነ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!