አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ለአፍሪካ ሀገራት አርአያ የሚሆን ሥራ እያከናወነች ነው አለ የአፍሪካ ቻይና ፖሊሲና ምርምር ማዕከል፡፡
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ፖል ፍሪምፖንግ በ2025 የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ጉባዔ ላይ እንዳሉት÷ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምሕዳር ግንባር ቀደም መሆን የሚያስችሉ ጠንካራ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲዎችን እየተገበረች ነው፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ ጠንካራ ፖሊሲን በመቅረጽ ቀጣይነት ያለው ሥራ እያከናወነች ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ ያላት ተሞክሮ በአፍሪካ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማስፋት ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ማዕከሉ በኢትዮጵያ ለ6 ወራት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለኢንዱስትሪ ልማት መሳለጥ የሚያስችሉ እድሎችን በተመለከተ ጥናት ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ በአዲስ አባባ የተካሄደው ጉባዔ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ሃሳብ እንዲሰጡ ማስቻሉን ጠቁመው÷ በዘርፉ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም ያመላከተ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ የፋይናንስ ዘርፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የግል ኩባንያዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና የዓለም አቀፍ አጋር አካላት መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ተሳታፊዎች የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ይበልጥ ለማሳደግ ድጋፍ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ ሥራ እያከናወነች መሆኑ የተነሳ ሲሆን÷ በዚህም ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት አርአያ መሆን እንደምትችል ተጠቁሟል፡፡
ዋና ዳይሬከተሩ የፕሮጀክቱ አላማ ከኢትዮጵያና ጋና የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የስኬት ምስጢሮችን በመቅሰም በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአፍሪካ አህጉር የአረንጓዴ ኢንዱስትሪን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!