አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜናዊ ኢራቅ በምትገኘው ሞሱል ከተማ ውስጥ ያለው አውሮፕላን ማረፊያ ተጠግኖ ዳግም በረራ ጀምሯል።
አውሮፕላን ማረፊያው ከ11 ዓመታት በፊት በአይኤስአይኤስ አሸባሪ ቡድን በመውደሙ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ቆይቷል።
የአውሮፕላን ማረፊያውን የመረቁት የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺያ አል-ሱዳኒ እንደተናገሩት፤ የአውሮፕላን ማረፊያው ዳግም ወደ ሥራ መመለስ የሞሱል ከተማን ከሌሎች የኢራቅ ከተሞች እና ከቀጣናው ሀገራት ጋር ያላትን ትስስር ያጠናክራል።
አውሮፕላን ማረፊያው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የተሟላ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ጠቁመዋል።
ከሶስት ዓመታት በፊት በኢራቅ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ አል-ካዲሚ አማካኝነት የአውሮፕላን ማረፊያው ዳግም ግንባታ መጀመሩን ያስታወሰው የኤኤፍፒ ዘገባ፤ አውሮፕላን ማረፊያው በአይኤአይኤስ አማካኝነት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ነበር ብሏል።
ከዚህ ቀደም በአብዛኛው ወደ ቱርክ እና ዮርዳኖስ የበረራ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው አውሮፕላን ማረፊያው ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ቆይቷል።
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!