አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን አፀደቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ያፀደቀው የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት ነው።
የተሻሻለው አዋጅ ሴቶች፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች በፖለቲካ የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጠናክር እንደሆነና ከዚህ ቀደም በነበረው አዋጅ በምርጫ ጣቢያ የነበረውን የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴን ወደ ምርጫ ክልል እንዲሆን ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።
የመራጮችን ምዝገባ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ እንዲሆን የሚያደርግ፣ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን ያካተተና በምርጫና በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሂደት የሚታዩ ክፍቶችን ሁሉ የሚሞላ እንደሆነም ተጠቁሟል።
የተሻሻለው አዋጅ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን የ6 ክልሎችን ድጋፍ ማግኘትን የሚያስገድድም ነው።
አዋጁ 1394/2017 ሆኖ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው ስብሰባ የፌደራል ገቢ ግብር ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ እና የስታርት አፕ ረቂቅ አዋጅን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በዙፋን ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
YouTube (http://www.youtube.com/@fanamediacorporation)