የሀገር ውስጥ ዜና

ከፍተኛ ዕውቀት፣ ሀብትና ልምድ የተገኘበት ህዳሴ ግድብ …

By Abiy Getahun

July 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕውቀት፣ ሀብትና ልምድ ያመጣ ፕሮጀክት ነው።

በመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ግንባታው በይፋ የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሺህ ያህሉ በተለያዩ ሙያዎች የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

የግድቡ የቴክኒካል ኮሚቴ አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያዊያን በሲቪል፣ መካኒካል፣ ሃይድሮሊክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፕሮጀክት አስተዳደር፣ በጉልበት ሥራ ተሳትፈዋል።

የባለሙያዎቹ ተሳትፎ ከፍተኛ የዕውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር በማስቻል የተፈተነ እና የዳበረ የግንባታ ዕውቀትና ልምድ እንዳስገኘ ጠቁመዋል።

ልምዱ እና ዕውቀቱ ተመሳሳይ ግዙፍ የግድብም ሆነ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አቅም ያለው የሰው ኃይል እንዲፈጠር ማስቻሉን ተናግረዋል።

ከተገኘው ዕውቀት በተጨማሪ ማህበራዊ ዕሴት እንዲዳብር አስችሏል ነው ያሉት።

ለአብነትም በግድቡ አቅራቢያ የጉባ ከተማ መፈጠርን ጠቅሰው፤ ከሁሉም አካባቢዎች የመጡ የግንባታ ሰራተኞች መሰባሰቢያ የሆነች ኢትዮጵያን የምትመስል ከተማ ናት ብለዋል።

በቴዎድሮስ ሳህለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!