የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር ለዘር ዝግጁ ተደርጓል

By Melaku Gedif

July 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በመኸር እርሻ እስካሁን 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት ለዘር ዝግጁ ተደርጓል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡

የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ÷ በክልሉ ለመኸር እርሻ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረትም እስካሁን 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለዘር ዝግጁ የተደረገ ሲሆን ÷ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታሩ ደግሞ በዘር ተሸፍኗል ብለዋል፡፡

በመኸር እርሻ ዋና ዋና ሰብሎችን ጨምሮ የአገዳ፣ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች እንደሚለሙ ጠቁመው÷ ከ368 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይ በአፋር ክልል በመኸር እርሻ 45 ሺህ ሔክታር በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ሃመዱ ሙሃመድ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በመኸር የሚለማው መሬት በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ÷ እስካሁንም ከ28 ሺህ ሔክታር በላይ ማሳ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡

በቆሎ፣ ጥጥና ሱፍን ጨምሮ የተለያዩ ሰብሎች በመኸር እርሻ የሚለሙ ሲሆን÷ ከ641 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም አብራርተዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!