አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጨማሪ የብርና ነሃስ ሜዳሊያዎች አግኝታለች፡፡
በናይጄሪያ አቡኩታ እየተካሄደ በሚገኘው ሻምፒዮና ሁለተኛ ቀን ውሎ በ3ሺህ ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች ውድድር ደስታ ታደለ 2ኛ እንዲሁም ብርነሽ ደሴ 3ኛ በመውጣት የብር እና ነሀስ ሜዳሊያ አስገኝተዋል፡፡
በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ እስካሁን 2 የብር እና ሦስት የነሃስ ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡