የሀገር ውስጥ ዜና

የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል – አቶ አወል አርባ

By sosina alemayehu

July 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል አሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፡፡

አቶ አወል በክልሉ የ2017 ዓም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የነበሩ ችግሮችን በመፍታት በርካታ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በክልሉ ጸጥታና ሰላምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው ÷ በተለይም የግብርና ሥራን በማከናወን ውጤት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት በሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስና ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ አመራሮች በ2017 ዓም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ለማጠናከር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በከሊፋ ከድር