አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቼልሲው የፊት መስመር ተጫዋች ኖኒ ማዱኬ በይፋ መድፈኞቹን ተቀላቅሏል፡፡
እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች እስከ ፈረንጆቹ 2030 በአርሰናል ቤት የሚያቆየውን የ5 ዓመት ኮንትራት ፈርሟል።
አርሰናል ለተጫዋቹ ዝውውር 52 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ አድርጓል።
ማዱኬ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውወር መስኮት ለአርሰናል አራተኛ ፈራሚ ሲሆን ከዚህ በፊት ዙቢሜንዲ፣ ኖርጋርድ እና ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ማስፈረሙ ይታወሳል።
ከፊርማው በኋላ ማዱኬ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ሁሉንም ዋንጫዎች ለማሸነፍ እንፋለማለን ያለ ሲሆን በአርሰናል በሚኖረው ቆይታ 20 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስም ተረጋግጧል።