የሀገር ውስጥ ዜና

የሠሜን ምዕራብ ዕዝ አባላት ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

By Abiy Getahun

July 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሠሜን ምዕራብ ዕዝ አባላት በጎንደር ከተማ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ችግኝ ተከላው ‘በመትከል ማንሰራራት’ በሚል መሪ ሀሳብ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካል መሆኑ ተገልጿል።

በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙት የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት፤ ሠራዊቱ የሀገሩን ሠላም እና ሉዓላዊነት ከመጠበቅ ባሻገር በልማት አጀንዳዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው።

የችግኝ ተከላው ሠራዊቱ ከህዝቡ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክርበት መሆኑንም ገልጸው፤ ሀገርን ለማጽናት ከሚደረገው ትግል ጎን ሁሉም ክፍለጦሮች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተሳትፎ ያደርጋሉ ነው ያሉት።

በዕለቱ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች እና የ502ኛ ኮር የሠራዊት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በበላይነህ ዘለዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!