የሀገር ውስጥ ዜና

በባቲ ከተማ በመኪና አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Adimasu Aragawu

July 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አቅራቢያ ለገተሚራ በሚባል አካባቢ በተከሰተው የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ቀን 5 ሰዓት አካባቢ በተከሰተው አደጋ አራት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው ሁለት ሰዎች ደግሞ ወዲያው ህይወታቸው እንዳለፈ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከባቲ ከተማ ፖሊስ ያገኘው መረጃ አመላክቷል።

አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ተገልጿል።

በከድር መሀመድ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!