የሀገር ውስጥ ዜና

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች አብሮነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ ያተኩራሉ

By Adimasu Aragawu

July 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ቆይታ የሚያደርጉ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አብሮነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ ያተኩራሉ አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ።

’’በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ 4ኛ ዙር የ2017 ዓ.ም የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ቡድን አባላት ዛሬ ማምሻውን ጋምቤላ ደርሰዋል።

ለወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አቀባበል ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሯ ሰላምን በማጽናት የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ከወጣቱ ኃይል የላቀ ድርሻ ይጠበቃል ብለዋል።

በተለይም እንደ ሀገር የተጀመረው የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰላምን ለማጽናት፣ በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነትና አንድነት በማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

በመሆኑም የዘንድሮ የወሰን ተሻጋሪ በጎፈቃደኛ ወጣቶች ቡድን ያገኙትን እድል በመጠቀም በቆይታቸው ከልማት ስራዎች በተጨማሪ አብሮነትና አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!