አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቬይትናም የቱሪስት ጀልባ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ37 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
አደጋው በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘውና የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ሃ ሎንግ ቤይ ነው የተከሰተው፡፡
አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ከዋና ከተማዋ ሃኖይ ለጉብኝት ወደ ሥፍራው ያቀኑ የሀገሪቱ ዜጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ፈልጎ ለማውጣት በሚደረገው ጥረት በአካባቢው እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ እንቅፋት መሆኑን የነፍስ አድን ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በተከናወነ የነፍስ አድን ሥራም 11 ሰዎችን ከውሃው በሕይወት ማውጣት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
መርከቧ 53 ሰዎችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን ፥ ድንገተኛ አውሎ ነፋስ ካጋጠማት በኋላ መገልበጧን የቬይትናም ድንበር ጠባቂዎች እና የባህር ኃይሎች አረጋግጠዋል፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!