የሀገር ውስጥ ዜና

በሌማት ትሩፋት 326 ሺህ ቶን ማር ተመረተ

By Melaku Gedif

July 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር 326 ሺህ ቶን ማር ተመርቷል አለ የግብርና ሚኒስቴር፡፡

የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የሌማት ትሩፋት ለማር ምርት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ባሕላዊ የንብ ቀፎዎችን ወደ ዘመናዊ ንብ ቀፎ በማሸጋገር ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም 2 ነጥብ 135 ሚሊየን ዘመናዊ የንብ ቀፎ ለማሰራጨት ታቀዶ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ዘመናዊ የንብ ቀፎ ማሰራጨት መቻሉን አመልክተዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት በማር አምራቾች ዘንድ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት በዘርፉ አመርቂ ውጤት አስገኝቷል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 296 ሺህ ቶን ለማመረት ታቅዶ 326 ሺህ ቶን ማር ማምረት መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ