የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ

By Hailemaryam Tegegn

July 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሰበታ ሃዋስ ወረዳ አስጀምሯል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በጎነት የኢትዮጵያውያን ባህል በመሆኑ ወደቀደመ የመተጋገዝ ዕሴታችን በመመለስ መረዳዳትን ተግባራችን ማድረግ ይገባናል።

ሚኒስቴሩ ከሚያከናውናቸው የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች መካከል የመኖሪያ መንደር እና የትምህርት ቤት ግንባታን ጨምሮ የሕብረተሰቡን ሕይወት መቀየር የሚችሉ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።

በዚህም ለ35 አባወራዎች ግንባታቸው በሦስት ወራት የሚጠናቀቅ ሞዴል የመኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ተጠቃሽ ነው።

በተጨማሪም በወረዳው ለሚገኙ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በሔብሮን ዋልታው