የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከሮተሪ ኢትዮጵያ አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Yonas Getnet

July 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከሮተሪ ኢትዮጵያ አመራሮች ጋር ትውውቅና ውይይት አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት፤ ተቋሙ በስነ ምግባር፣ በጤናና በተለያየ መስክ እየሰራ ያለዉ ተግባር የሚበረታታ ነው፡፡

ይህ ስራ በሕብረተሰቡ ዘንድ የበለጠ እንዲታወቅ መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡