የሀገር ውስጥ ዜና

ማሰልጠኛ ማዕከሉ ከብልጽግና ጉዟችን ጋር አብሮ የሚራመድ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

By Melaku Gedif

July 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የቢሾፍቱ ማሰልጠኛ ማዕከል ከብልጽግና ጉዟችን ጋር አብሮ የሚራመድ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የማሰልጠኛ ማዕከሉን የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የስልጠና ክፍሎችን እና የስልጠና ማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅትም ኢንስቲትዩቱ ለረጅም ዓመታት የመንግስትና የግል ዘርፉን በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ሙያተኞችን አቅም በመገንባትና በማብቃት ለበርካታ ዓመታት ጉልህ አሻራውን አሳርፏል ብለዋል።

የመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደርን ለማሻሻል የተጀመረውን ሪፎርም በመደገፍ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ተቋም እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የቢሾፍቱ ማሰልጠኛ ማዕከል ለበርካታ ተቋማት ስልጠና በመስጠት፣ በማማከር እና በዘርፉ ምርምር በማድረግ ላይ የሚገኝ ውብ የአረንጓዴ ገጽታ እና ሰፊ ግቢ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

ማዕከሉ ከብልፅግና ጉዟችን ጋር አብሮ የሚራመድ ብቻ ሳይሆን የመንግስትን እና የግል ዘርፉን ተቋማዊ ለውጥ እና የመፈፀም አቅም ለማጎልበት የለውጥ አርዓያ መሆን አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ሀገራዊ መሻትን ያገናዘቡ፣ በሰልጣኞች ዘንድ እውቀትን፣ ሀሴትን እና የለውጥ ቁጭትን የሚፈጥሩ ምቹ የማሰልጠኛ፣ የሰልጣኞች ማደሪያና የመዝናኛ ክፍሎችን እንዲገነባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

የፌደራል መንግሥት የሥልጠና ማዕከሉን ለማዘመን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!