የሀገር ውስጥ ዜና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 51 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተሰበሰበ

By Melaku Gedif

July 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ከመኸር አዝመራ 51 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተሰበሰበ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በም/ቤቱ የቀረበውን የ2017 በጀት የግብርና አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷በዓመቱ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ ንቅናቄዎችን በመተግበር በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል፡፡

በክልሉ ዘመኑን የዋጁ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በተከናወኑ ሥራዎችም ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት፡፡

‎‎በመኸር እርሻ 559 ሺህ 592 ሔክታር መሬት በማልማት ከ51 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን ሃላፊው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ ከላይኛው አመራር እስከ አርሶ አደሩ የተደረገው ክትትልና ድጋፍ ለውጤታማነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመልክተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም አርሶ አደሩ ሜካናይዜሽንን እንዲያስፋፋ እና የግብዓት አቅርቦት በወቅቱ እንዲያገኝ በትኩረት መሰራቱን ነው ያስረዱት፡፡

በተለይም የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር በሁሉም አካባቢዎች በሚፈለገው መጠን በወቅቱ ተደራሽ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

በክልሉ በሌማት ትሩፋት፣ በመስኖ ልማትና ሌሎች ንቅናቄዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይም በአርሶ አደሩ ዘንድ የተፈጠረውን አዲስ የሥራ ባህል በማጠናከር ምርታማነቱን እንዲያሳድግና ሕይወቱን እንዲያሻስል በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!