አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 49 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን በሩሲያ ምስራቃዊ ክፍል አሙር ግዛት ከራዳር ውጪ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ደብዛው የጠፋው አውሮፕላኑ አምስት ሕጻናትን ጨምሮ 43 መንገደኞችንና 6 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ እንደነበር የአሙር ግዛት አስተዳዳሪ ቫስሊ ኦርሎቭ ተናግረዋል፡፡
አንቶኖቭ ኤኤን-24 የተሰኘው የመንገደኞች አውሮፕላን ከአሙር ግዛት ብላጎቨሽቼንስክ ወደ ቲይንዳ እያመራ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አሁን ላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች ደብዛው የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለግ ሒደት መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!