አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሩሲያ ምስራቃዊ ክፍል አሙር ግዛት በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ በደረሰ የመከስከስ አደጋ የ49 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የሩሲያ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት አመራሮች እንዳሉት÷ በዛሬው ዕለት 49 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን በሩሲያ ምስራቃዊ ክፍል አሙር ግዛት አካባቢ ከራዳር እይታ ውጪ ሆኖ ተከስክሷል፡፡
በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አምስት ሕጻናትን ጨምሮ 43 መንገደኞችና 6 የበረራ ሠራተኞችን በአጠቃላይ የ49 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡
አንቶኖቭ ኤኤን-24 የተሰኘው የመንገደኞች አውሮፕላን ከአሙር ግዛት ብላጎቨሽቼንስክ ወደ ቲይንዳ አውሮፕላን ማረፊያ እያመራ እንደነበር ሞስኮው ታይምስ ዘግቧል፡፡