አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር በተለያዩ የሥራ በኃላፊነቶች ያገለገሉት ግራዝማች አያሌው ደስታ በ103 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ማህበሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መረጃ፤ ግራዝማች አያሌው ደስታ ሀገራቸውን በአርበኝነት ያገለገሉ ለሰላም እና አንድነት በትጋት የሰሩ ጀግና ነበሩ፡፡
የጥንታዊት ኢትዮጰያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንዔል ጆቴ መስፍን፤ አርበኛ ግራዝማች አያሌው ደስታ በተደጋጋሚ የማህበሩ ምክር ቤት አባል በመሆን ማገልገላቸውን አስታውሰዋል።
ከሌሎች አርበኞች ጋር በቅንጅት በመሆንም ለሀገራቸው ክብር የተዋደቁ ስለመሆናቸው ነው የተናገሩት፡፡
አርበኛ ግራዝማች አያሌው ደስታ ለማህበሩ መጠናከር እና የእስካሁን ጉዞ ከፍተኛ ሚና መወጣታቸውን ያስታወቀው ማህበሩ፤ ለግራዝማች አያሌው ደስታ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!