አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች አጀንዳ በመጠቆምና ተወካዮቻቸውን በመመረጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጥበቡ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ በአፍሪካ አህጉር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በዙም ውይይት ይደረጋል፡፡
የዳያስፖራውን ማህበረሰብ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ተሳታፊ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፥ በዙም በሚደረገው ውይይት ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ዝግጅቱን አጠናቅቋል ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቀጣይ ሳምንት ሀሙስ በሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ከታች በተቀመጠው ሊንክ ላይ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
በአቤል ንዋይ